
የአረመኔው የአብይ አህመድ ፋሽስት ሰራዊት በወጣት አርበኛ ሴቶቻችን ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ጥግ መላው ዓለም ሊያውቀውና ሊያወግዘው ይገባል!!!
የፋኖ ሰራዊት የጠላት ወታደር ቁስለኛ ምርኮኛ በቅድሚያ ህክምና እንዲያገኝ ሲያደርጉ፣ ሌላውም ምርኮኛ ደግሞ በምህረት ወደ ቤተሰቦቹ እንዲሄዱ ያደርጋሉ። ምርኮኞች ቁጥራቸው በርከት ሲልም ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልን በመጠየቅ እንዲረከባቸው ያደርጋሉ። የታወቀውን የዓለም አቀፍ ምርኮኛ አያያዝን ህግ ያከብራሉ። ይህ በፋኖ ዘንድ የተለመደ አሰራር ነው።
የ 19 ዓመትዋ ወጣቷ በዓለም ዋሴ እንደማንኛውም ወጣት የራሷን ኑሮ አመቻችታ እንደ ከሌላው ወጣት ጋር ተመሳስላ መኖር ትችል ነበር፤ ሆኖም ግን በአማራው ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ሰቃይና መከራ፣ ሰደትና መፈናቀል፣ መገደልና መጨፍጨፍ አንገብግቧት ይህን አረመኔ የአብይ አህመድ ፋሽስት አገዛዝን ለመፋለምና ነጻነቷን ለማስከበር ቆርጣ ወስና የህልውና ትግል ከሚያደርገው ፋኖ ጋር በአርበኝነት ተቀላቀለች። በፋኖም ውስጥ የመደበኛና የኮማንዶ ስልጠናዎችን ጨርሳ የአፋብኃ ቲዎድሮስ እዝ 5ኛ ክፍለ ጦር አባል ሆና ከሌሎች ጓዶቿ ጋር ለቅኝት ሰራ ተሰማርታ እያለ ድንገት በአረመኔው የአብይ አገዛዝ ወታደሮች ቀለበት ውስጥ ወደቀች። ጥቂት አርበኞች ሆነው የሚችሉትን ያህል ቢዋጉም የአብይ አህመድ ወታደሮች በርካታ ነበሩና ጥቅምት 2 ቀን 2018 በጥይት ቆስላ ተማረከች።